ማስታወቂያ
በፓሪስ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ኤምባሲ በማድሪድ ከተማ በመገኘት በስፔን ሃገር ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የቆንስላ፣የኢምግሬሽን እና የዳያስፖራ አገልግሎቶችን ይሰጣል።
በመሆኑም ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አስፈላጊውን መረጃ በማዘጋጀት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንድትሆኑ ኤምባሲው ጥሪ ያስተላልፋል።
የሚሰጡ አገልግሎቶች፡-
የፓስፖርት ዕድሳት፣ እርማት፣ የጠፋ ፓስፖርት ምትክ፤
የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ማውጣት፣ እድሳት፤
ከወንጀል ነጻ ማረጋገጫ፤
ውክልና፤
ሰነድ ለማረጋገጥ፤
የግብር ከፋይ መለያ (TIN) ቁጥር አሻራ አገልግሎት፤
የጠቅልሎ ተመላሽ የቀረጥ ነጻ፤
በሀገር ቤት ለጡረታ ተጠቃሚዎች በሕይወት መኖርን ስለማሳወቅ፤
የዳያስፖራ ኢንቨስትመንት ድጋፍ፤
የውጭ ምንዛሬ አካውንት (Diaspora Account) ድጋፍ፤
ቀን፡- እ.ኤ.አ. May 16 እና 17 ቀን 2026 (ግንቦት 09 እና 10 ቀን 2018)
ሰዓት፡- May 16 ከ 9፡00 እስከ 17፡00 እና May 17 ከ9:00 እስከ 12:00 በስፔን ሰዓት አቆጣጠር
ቦታ፦
- Hotel Crown Plaza Retiro
- C/ Pez Volador 1. 28007 Madrid, Spain Como llegar pincha aqui
- Metro: Linea 6
- Parada Sainz de Baranda
ማስታወሻ፡- አገልግሎት ለማግኘት መሟላት የሚያስፈልጉ ሰነዶችን የቀረበውን QR Code ወይም ሊንክ በመጠቀም መመልከት ይችላሉ።
በተጨማሪም ፓስፖርትን ጨምሮ በኢምባሲው የሚገኝ ሰነድ ካሎት በእለቱ መረከብ ይችላሉ

